የ1% አስተዋፅኦ የህይወት ዘይቤ እንቅስቃሴ
የ1% አስተዋፅኦ የህይወት ዘይቤ እንቅስቃሴ እያንዳንዱ ሰው ቤተሰቡን፣ ማህበረሰቡን፣ ሀገሩን እና አለምን ለማሻሻል ከጊዜው፣ ከእውቀቱ፣ ከክህሎቱ፣ ከሀብቱ፣ ከተፅዕኖው ወይም ከደግነቱ ጥቂት ክፍል እንዲያበረክት ያነሳሳል። የእርስዎ አስተዋፅኦ ፍፁም ወይም በጣም ግዙፍ መሆን የለበትም። ወጥ የሆነ (ተደጋጋሚ) መሆን ብቻ ነው የሚጠበቅበት። ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች 1% አስተዋፅኦአቸውን ሲሰጡ፣ ትንንሽ እርምጃዎች ለለወጥ የሚሆኑ ታላቅ ኃይል ይሆናሉ። • የእርስዎ እውቀት ዋጋ አለው። • የእርስዎ ታማኝነት ዋጋ አለው። • የእርስዎ ስራ ዋጋ አለው። • የእርስዎ ደግነት ዋጋ አለው። • የእርስዎ አርአያነት ዋጋ አለው። The 1% Contribution Lifestyle Movement inspires every person to contribute a small part of their time, knowledge, skills, resources, influence, or kindness to improve their family, community, nation, and the world. Your contribution does not have to be perfect or enormous. It only needs to be consistent. When millions of people give their 1%, small actions become a powerful force for change. Your knowledge matters. Your honesty matters. Your work matters. Your kindness matters. Your example matters.
ከመሥራቹ ጋር ይተዋወቁ
ለዚህ እንቅስቃሴ መነሻ የሆነው ጥያቄ ለብዙ ዓመታት ሰዎች በዙሪያቸው ባሉ ችግሮች—በትምህርት ጥራት ማነስ፣ በሥራ አጥነት፣ በታማኝነት ማጣት፣ በማኅበረሰብ መላላትና በከንቱ በሚያልፉ ዕድሎች ላይ ሲያማርሩ እታዘብ ነበር። እኔም ብሆን አማርር ነበር። ነገር ግን አንድ ቀን እንዲህ ብዬ ራሴን መጠየቅ ጀመርኩ፦ «ለመፍትሔው እኔ በግሌ ምን አስተዋፅኦ እያደረግኩ ነው?» ያ ጥያቄ አስተሳሰቤን ለወጠው። ሁሉንም ችግር መፍትሔ መስጠት ላይችል እችላለሁ፤ ነገር ግን አንድ ነገር ማበርከት እንደሚቻል ተረዳሁ፦ እውቀቴን፣ ጊዜዬን፣ ልምዴን፣ ድምፄን ወይም ደግሞ አንድ ትንሽ ጠቃሚ መልካም ተግባር። ከዚያም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ተመሳሳይ ውሳኔ ቢወስኑ ምን ሊፈጠር እንደሚችል በኅሊናዬ ሳልኩት። ያ ሐሳብ የ1% የመዋጮ/የአስተዋፅኦ ሕይወት ዘይቤ እንቅስቃሴ ሆነ። ይህን እንቅስቃሴ የጀመርኩት፣ ለውጥ የሚጀምረው በእጃችን ያለውን ነገር መጠቀም ስንጀምር ነው ብዬ ስለማምን ነው። የእያንዳንዳችን አስተዋፅኦ ለብቻው ሲታይ ትንሽ ሊመስል ይችላል፤ ነገር ግን ቤተሰቦችን፣ ማኅበረሰቦችን፣ አገሮችንና መጪው ትውልድ የሚረከባትን መጻኢ ጊዜ መለወጥ እንችላለን። የእኔ 1% ዋጋ አለው። የእርስዎም 1% ዋጋ አለው። Meet the Founder The Question That Inspired This Movement For years, I watched people complain about the problems around them—poor education, unemployment, dishonesty, weak communities, and lost opportunities. I also complained. But one day, I began to ask myself: “What am I personally contributing to the solution?” That question changed my thinking. I realized that I might not be able to solve every problem, but I could offer something: my knowledge, my time, my experience, my voice, or one small helpful action. Then I imagined what could happen if millions of people made the same decision. That idea became the 1% Contribution Lifestyle Movement. I created this movement because I believe change begins when we stop waiting for someone else and start using what we already have. Our individual contributions may appear small, but together they can transform families, communities, nations, and the future inherited by the next generation. My 1% matters. Your 1% matters.
